ምርጫ ቦርድ የባልደራስን ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ አደረገው

የአ/አ ህዝብን በዘለፉት ዘላለም ሙላቱ ጉዳይ፣ ባልደራስ ቀጣይ እርምጃውን ሊያሳውቅ ነው

አቶ ዘላለም ሙላቱ የተባሉ የገዥው ፓርቲ ካድሬ የአዲስ አበባን ሕዝብ ‘ፈርሳምና ከርሳም’ በማለት በከተማው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ጉባዔ ላይ መዝለፋቸውን ተከትሎ፣ ከምክር ቤት የሚነሱበትን እንቅስቃሴ ለማስጀመር ህጋዊ ቅፅ እንዲያዘጋጅ የተጠየቀው ምርጫ ቦርድ፣ ጥያቄውን ለሁለተኛ ግዜ ውድቅ አድርጎታል ። ባልደራስ ጥያቄውን አብራርቶ ባቀረበው አቤቱታ፣ ” ፊርማ ካሰባሰብን ቦኃላ ያላሟላው ነገር አለ ተብሎ ውድቅ እንዳይሆን፣ ምርጫ ቦርድ የሚያሰፈልጉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ቅፅ ከወዲሁ አዘጋጅቶ ይስጠን” ሲል ከአንዴም ሁለቴ ጠይቋል።

የመጀመሪያው አሉታዊ ምላሽ ጥያቄውን በትክክል ካለመረዳት የመነጨ ሊሆን ይችላል በሚል እሳቤ ፓርቲው ጥያቄውን በድጋሜ ቢያቀርብም ቦርዱ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ አድርጎታል።

ይህን ተከትሎ፣ ቀጣይ እርምጃውን ፓርቲው በመጪው ሳምንት እንደሚያሳውቅ ለማወቅ ተችሏል።