የስነልቦና ጉዳት ስለደረሰብን ምስክር የመስማት ፍላጎት የለንም ስለዚህ ረጅም ቀጠሮ ይሰጠን – አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ)

” የስነልቦና ጉዳት ስለደረሰብን ምስክር የመስማት ፍላጎት የለንም ስለዚህ ረጅም ቀጠሮ ይሰጠን ” ሲሉ እነ አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ፍርድ ቤቱን ጠየቁ።

” ከሌሎች የተለየ ወንጀልሳንሰራ ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም ” በማለት 2 ቀጠሮ የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ኡመርን ጨምሮ 11 ተከሳሾች ችሎት ሳይቀርቡ ቀርተው ነበር።

ዓቃቤ ህግም ተገደው እንዲቀርቡ አልያም በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ችሎቱን ጠይቆ ነበር።

ፍርድ ቤቱ መርምሮ በጉዳዩ ላይ ትዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን፤ ነገር ግን በዛሬው ቀጠሮ ሁሉም ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተከሳሾቹም የስነ ልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ባሉበት ሁኔታ ምስክር የመስማት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጽ እረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ከሳሽ ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ጥያቄያቸው ከህግ አንጻር አሳማኝ አደለም ሆኖም እረጅም ቀጠሮ ቢሰጣቸው እንደማይቃወም አብራርቷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ ቀሪ የአቃቢህግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 19 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ