የኮሚሽነሮች ምርጫ ጉዳይ እያነጋገረ ነው ።

የኮሚሽነሮች ምርጫ ጉዳይ በማሕበራዊ ሚዲያ እያነጋገረ ነው ።  የተወሰኑትን ለመመልከት እንሞክራለን ።

ከኢዜማው ዮሃንስ መኮንን እንጀምር

ሀገራዊ ምክክሩን እንዲመሩ ቀድሞ ለሕዝብ ይፋ ከተደረጉት 42 እጩ ኮሚሽነሮች ዝርዝር ውስጥ ስማቸው የሌለ ነገርግን ዛሬ ይፋ የተደረጉት 11 ውስጥ የተካተቱት ሦስት ኮሚሽነሮች አሉ።
1) ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ
2) ወ/ሮ ብሌን ገብረ መድኅን
3) አቶ ሙሉጌታ አጎ
ከጠቅላላ 632 ተጠቋሚዎች 42 ተለይተው የተመረጡበት መስፈርት ለሕዝብ ግልጽ እንዲደረግ እየወተወትን እያለ ይግረማችሁ ብሎ ይፋ ከተደረጉት 42 ውስጥም የሌሉ 3 ተሿሚዎችን መጨመር የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ነጻነት እና ተአማኒነት ላይ ቀዝቃዛ ውኃ እንዳይቸልስበት እሰጋለሁ!
Yohannes Mekonnen – ዮሐንስ መኮንን

አበበ ቀስቶ የተባሉ በፖለቲካው ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ግለሰብ እንደጻፉት

የኮሚሽነሮች ምርጫ ጉዳይ ??
ሶስቱ ከየት መጡ ???
ዛሬ በሕ/ተ/ም/ቤት ከተሾሙት (ከተመረጡት ) ኮሚሽነሮች ሶስቱ
1ኛ/..ወ/ሮ ብሌን ገ/መድህን
2ኛ/..አቶ ሙሉጌታ ኦጎ
3ኛ/..ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ
መጀመሪያ ለሕዝብ ይፋ ከሆኑት 42 የኮሚሽነር ዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ የሉም ከየት መጡ ??
እንዴት መጡ ??
ተፎካካሪ ፓርቲዎች በዕጩዎች አመራረጥ ላይ ቅሬታ አለን ሲሉ በጋራ ም/ቤቱ 45 ፓርቲዎች መግለጫ አውጥተው ነበር።
ዛሬ ተወካዮች ም/ቤት አመራረጡ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ተሳትፎ አለበት ማለቱ ከተዓማኒነት አንፃርና ከመተማመን አንፃር ምን ያህል ያስኬዳል ?? ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል ።
አጥናፍ ብርሃነ የተባሉ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ የነበሩ በትዊተር ገጻቸው የሚከተለውን ብለዋል።

ፈጣሪውም፣ አድራጊውም፣ ሿሚውም፣ አስረጅውም….. የብልጽግና ፓርቲ የሆነበት ግልጽነት የጎደለበት አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ያለው ምንሊክ ሳልሳዊ ነው።

በርካቶች በማሕበራዊ ሚዲያ በተለይ ፌስቡክ ላይ የኮሚሽነሮችን ምርጫ እየተቃወሙ፤ ጥያቄም እየጠየቁ ይገኛሉ ።

May be an image of text

No photo description available.