ጠ/ሚ ጥሩ ተናግረዋል፤ ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው በህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካና ኢኮኖሚ መስራት ሲችሉ ነው።

ሕዳሴ ግድብ ኃይል በማመንጨቱ እንኳን ደስ አለን !

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሩ ተናግረዋል። ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው በቅድሚያ ራሳቸውንና ፓርቲያቸውን ከፖለቲካ ንግድ አውጥተው በህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካና ኢኮኖሚ መስራት ሲችሉ ነው። ትላንት የተናገሩትን ዛሬ ረስተው ነገ ሌላ በማውራት የሚመጣ ዘላቂ ሰላም የለም። እንዴት ልሸውድ የሚል የፉገራ ፖለቲካ ሊቆም ይገባል።

ፖሊሲዎች ሲሻሻሉ፣ ሚኒስትሮች ከሃሰት ሪፖርት ሲወጡ፣ ካድሬዎች ብልጽግና እና ብልግናን ሲለዩ፣ ህግና ደንብ ሲከበር፣ ባለስልጣናት ከማናለብኝነት ሲላቀቁ፣ በህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ሲኖር፣ ኢኮኖሚውን መንግስት በህዝብ ልክ ሲሰራው፣ የተማሩና አደርባይ ያልሆኑ ምሁራን የመንግስት አማካሪ ሲሆኑ ፣ ካድሬዎች ለተግባራዊ ስራ፣ ለልማትና ሰላም ሲሰማሩ፣ በዘፈቀደ እስርና መገፋት ሲቆም፣ የህግ የበላይነት ሲሰፍንና ፖለቲካው ከፍትሕ ስርዐቱ ላይ እጁን ሲያነሳ፣ መንግስትከፖለቲካ ንግድና ከማምታታት ሲወጣ…. የመሳሰሉት ሲከወን …….

…… ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ከዚህ በኋላ ከጥቃቅን አጀንዳ እርስ በእርስ ከመበላላት ፤ከእርስ በእርስ ሽኩቻዎች ወጥተን ተደምረን ተሰባስበን እንደ ህዳሴ ኢትዮጵያን እንድንሰራ ፤ ከመናቆር ከማያስፈልግ ከተንኮል ፖለቲካ እንድንወጣና ፤በይቅርታ ልብ በጋራ እንድንቆም ፤ተባብረን ሃገራችንን እንድናለማ ለሁላችንም በጎና ቅን መንገድ ይከፍታል። ይህ የሚተገበረው ጠቅላዩ መጀመሪያ እንደ ገዢ ፓርቲ ራሳቸውንና ፓርቲያቸውን መለወጥ ሲችሉ ብቻ ነው።

ይህ ሊሆን የሚችለው በቅድሚያ መንግስት ራሱን ሲፈትሽ፣ ዜጎች በሰላም ደሕንነታቸው ተጠብቆ በነጻነት መኖር ሲችሉ ነው። ይህ ባሌለበት ባለስልጣናት በማናለብኝነት በሕዝብ ላይ ሲደነፉና የህዝብን መብት እየጣሱ ባለበት ሂደት ህዝብ በዝምታ ውስጥ ይሆናል ዝምታው የፈነዳ እለት ደግሞ መሪዎቹን ይበላል። መንግስት ሊያስብበት ይገባል። #MinilikSalsawi