አዲስ አበባ በዐማራ ስደተኞች በመጥለቅለቅ ላይ ትገኛለች።

Zemedkun Bekele – ነጭ ነጯን – ስደት ወደ አዲስ አበባ ጨምሯል !!

“…የአዲስ አበባ ከተማ በአሁን ሰዓት ከኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ነፃ አውጪዎች የታረዱት ታርደው፣ ሀብት ንብረታቸውንም ተዘርፈው እንደ ዕድል ከመታረድ ያመለጡቱ ዐማሮች ወደ አዲስ አበባ በብዙ ቁጥር እየጎረፉ ይገኛሉ። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባም በዐማራ ስደተኞች በመጥለቅለቅ ላይ ትገኛለች።
በድኑ ብአዴን፦ እስከ አሁን ይሄን ሁሉ አልሰማም። ደመቀ መኮንን ከዲሲ ግብረ ኃይል ጋር ውይይት ላይ ነው። ብናልፍ አንዷለም የለም። ገዱ አንዳርጋቸው አያገባኝም ብሏል። ላቀ አያሌው የገቢ ወጪ ሂሳብ ቆጠራ ላይ ነው። አቶ አብርሃም ስብከት እያዘጋጀ ነው። አቶ አገኘሁ 9 ሚልዮኗን ለአረቄም፣ ለካቲካላም እያለ እያባከናት ነው። ዳግማዊት ሁለተኛ ቪላዋን ቀለም እያስቀባች ነው። በአጠቃላይ ብአዴኖች የሉም። አቶ ንጉሡም የታፈኑትን ልጆች መልሶ አሳፍኖ አሁን ከጃዋር ጋር ስብሰባ ላይ ነው።
“…ዐብን፦ ዐብን ሊቀመንበሩ ቤልጅየም ከአቢቹ ጋር ስብሰባ ላይ ነው። ወዳጄ የሱፍ ኢብራሂም የአዲስ አበባ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስለተደረጉ “የድግስ ዕቃ” ቆጠራ ላይ ነው። ጣሂሮ ኮሚሽነር ከሆነች ወዲህ ደብዛዋ ጠፍቷል። ክርስቲያን ታደለ ብቻውን እንደ በረሃ ሸንበቆ ከወዲያ ወዲህ ይወዛወዛል። ዐቢይ አሕመድና አንዳርጋቸው ጽጌ ዐብንን በ12 ቁጥር ሚስማር ጠብስቀው ጠርቅመው ውልፍትም እንዳይል ኮዋሻኮር እንዳጠቃው ሰው ሽባ ልምሾ አድርገው አስቀምጠውታል። ዐብኖችም አልሰሙም።
May be an image of 11 people, people sitting, people standing and outdoors“…ባልደራስ፦ የባልደራሱ እስክንድር ነጋ ፓርቲ ብቻ ነው አሁን በእነዚህ ስደተኞች ጉዳይ ከወዲያ ወዲህ የሚባዝነው። ሚዲያዎች የዩቱዩብ ቻናላቸው እንዳይዘጋ፣ ፈቃዳቸውንም እንዳይቀሙ ጮጋ ብለዋል። ታዋቂ ሰዎች፣ ከሂዊ ጋር ጦርነት ሊገጥሙ ግንባር ድረስ ሄደው ፎቶ ተነሥተው የመጡት አርቲስቶችም ጭምር የበላቸው ጅብ አልጮህ ብሏል። ብልጽግና ሃገር መምራት አለመቻሉን በደንብ አስመስክሯል። ስደቱ እንደሁ ለማንም አይቀርም። ዝምታም መፍትሄ አይሆንም። ቢያንስ መነጋገር መፍትሄ ይኖረዋል።
“…ዳያስጶራ የዐቢይ መንግሥት ፍቅር አልወጣለት ብሎ ተጨንቋል። ኤችአር ምንትስዬ እንዳይፀድቅ ሰልፍ ሊወጣ ባንዲራ፣ መፈክርና ቲሸርት በማዘጋጀት ላይም ይገኛል። ዳይስጶራ በተለይ የጌታ ልጆች ዐቢያቸው፣ ነቢያቸው እንዳይነካ፣ ከዙፋኑም እንዳይናወጽ ጾም ጸሎት ዐውጀው እየደከሙ መሆናቸው ተሰምቷል።
“…ወንድ ልጅ ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ ማየት ከፈለጋችሁ የካ ሚካኤል፣ ፈረንሳይና ጃንሜዳ ሂዱ። ህጻናት ሲያለቅሱ፣ አዛውንቶች ርቧቸው ሲቃትቱ ለማየት ጎራ በሉ። ስደቱ ለሁሉም የማይቀር ስለሆነ ስደተኛ ስቃዩ ምን እንደሚመስል ከወዲሁ ልምድ ቅሰሙ። ብልፅግናን ስለመረጥክ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ ወላይታ ወዘተ ስለሆንክ አታመልጥም። የማን ቤት ፈርሶ የማን ቤት ይለማ መስሎሃል። እኩል ትራባታለህ፣ እኩል ትጠማታለህ፣ እኩል ትሰደዳታለህ። ይኸው ነው። እኩል አልኩህ። ሌላኛው ዐማራ ግን… ጸልይ፣ ስካርህን ተው፣ ተመካከር፣ ተሰባሰብ፣ ተነጋገር። ጊዜው ለአንተ ከባድ ነው። የተኛህም ንቃ።
“…የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቶአል፤ ምሽግን ጠብቅ፥ መንገድንም ሰልል፤ ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ።” ናሆ 2፥1

May be an image of 2 people, people standing, people sitting and outdoors