የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ያቀረበው ክስ ታወቀ

የቀድሞው የብረታብረት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ዕየታየ ነው
የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በተጠርጠሪው ላይ የቀረበው የአቤቱታ መዝገብ ዋና ዋና ነጥቦች

• ሜቴክ ባሉት 10 ኢንደስትሪዎች ድጋፍ እንዲሰሩ የተያዙ ፕሮጀክቶችን ማጓተት
• ያዩ ማደበርያ
• የስኮር ፋብሪከዎች
• የታለቁ የህዳሴ ግድብ
በዚህ ሳቢያም የህዝብና የመንግስት ንብረት እንዲባክን ማድረግ

• የጨረታ ህግን በመጣስ ጨረታ ስራ ያጓትታል በሚል ያለ ጨረታ ህገወጥ ግዢ መፈፀም

• ከኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት አገልግሎት 28 ዓመት በማገልገላቸው ለሜቴክ ብረታቸው ቀልጦ ለግብአትነት እንዲውሉ የተሰጡ መርከቦችን የስራ ኃላፊው ያለሙያቸው በመግባት ከ29 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ ተጠግነው በህገወጥ መልኩ ለንግድ አገልግሎት ስራ ላይ እንዲውሉ አድርገዋል ፤

በኋላም መርከቦቹን በ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር እንዲሸጡ አድርገዋል ፤ለጥገናም ወጪ ቢያስወጡም ስራ ላይ ሲሰማሩም ሆነ በመጨረሻ ሲሸጡ መርከቦቹ ለሀገሪቱ አንድም ሳንቲም ገቢ አላስገቡም በዚህም በሀገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል

• ለያዩ ማደበሪያ ከተያዘው 11 ቢለየን ብር 25 በመቶውን 2.5 ቢሊየን ብር ሜቴክ ቢወስድም ምንም ስራ አልሰራም