በቤንሻንጉል በፌዴራሉ መንግሥትና አማጽያን መካከል በተቀሰቀሰ ውጊያ የስደተኞች ካምፕ ተቃጠለ ተዘረፈ – ተመድ

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) እና አጋሮቹ በኢትዮጵያ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ያሉትን ስደተኞች ለመርዳት እየተረባረቡ ነው ሲሉ፣ የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ቦሪስ ቼስሺርኮቭ ጄኔቭ ላይ ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

እኤአ ጥር 18 ቶንጎ በተባለው ከተማ በፌዴራሉ መንግሥትና አማጽያን መካከል በተቀሰቀሰ ውጊያ በአቅራቢያው የነበረውና ወደ 10ሺ300 የሚደርሱ ስደተኞችን የሚያስተናግደው መጠለያ ካምፕ መቃጠልና መዘረፉንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

በሌላኛው መጠለያም ላይ በደረሰ ተመሣሳይ ጥቃት በድምሩ ወደ 22ሺ የሚደርሱ ስደተኞች እርዳታ ከሚያገኙበት ስፍራ መነጠላቸውን ገልጸዋል፡፡

ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የገለጹት ቃል አቀባዩ ወደ 70ሺ የሚደርሱ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ስደተኞ የሚገኙ ሲሆን፣ 500ሺ የሚደርሱ የአገር ውስጥ ተፈናቃይ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

UNHCR, the UN Refugee Agency, and partners are rushing life-saving aid to more than 20,000 refugees after they fled clashes in Ethiopia’s Benishangul Gumuz region, bordering Sudan and South Sudan. Fighting broke out on 18 January in the town of Tongo – reportedly between unidentified armed groups and federal forces – and the nearby camp hosting 10,300 refugees was looted and burned. This followed the looting of another camp in the area in late December. A total of 22,000 people in both camps were then cut off from access and assistance. All humanitarian staff had to evacuate, and access to the area including the two camps – Tongo and Gure-Shembola – remains impossible. Since December last year the situation has been very tense in the Benishangul Gumuz region, which hosts more than 70,000 Sudanese and South Sudanese refugees and over 500,000 internally displaced Ethiopians.

የቤንሻንጒል ክልል አስተዳደር እስከ 20ሺ ስደተኞችን ማስፈር የሚችሉ አዳዲስ የመጠለያ ስፍራዎችን በመስጠት ትብብር ማሳየቱን ገልጸው፣ ኮሚሽኑ መሠረታዊ የሆኑ የመጠለያና የውሃ የመሳስሉትን አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ፣

የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ኤሪ ካኔኮ ትላንት በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ አፋር ክልል የሚካሄደው ግጭት በትግራይ ክልል እየጨመረ ላለው የሰብአዊ እርዳታ የሚሰጠው ምላሽ ወደ ክልሉ እንዳይገባ መሰናክል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በተነሳ ግጭት ከ200ሺ በላይ ስደተኞች መፈናቀላቸውንም ገልጸዋል፡፡

በግጭቱ የተነሳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ አጋሮቻችን በአካባቢው ያለውን የችግር መጠን ለመገምገም ተቸግረናል ሲሉም ቃል አቀባዩዋ ተናግረዋል፡፡

ተደራሽነቱ ክፍት በሆነበት በአፋር ክልል 40ሺ የሚደርሱ ሰዎች ባለፈው ሳምንት የምግብ እርዳታ ያገኙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ አካባቢ ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ ከ420ሺ ሰዎች በላይ እርዳታ ማዳረስ መቻሉንም ቃል አቀባይዋ ገልጸዋል፡፡

https://www.unhcr.org/news/briefing/2022/2/61fcf1f04/unhcr-partners-rush-aid-thousands-refugees-benishangul-gumuz-region-ethiopia.html