የጉራጌ ህዝብን ሴማዊነት ለኦሮሙማ የመሸጥ ቁማር በታሪክ ሲፈተሽ

[addtoany]

የጉራጌ ህዝብን ሴማዊነት ለኦሮሙማ የመሸጥ የነርስቱ ይርዳው ቁማር በታሪክ ሲፈተሽ

የጉራጌ ህዝብ ጉርአ ከሚባለው የትግራይ አካባቢ ወደ መሐል አገር በመምጣት ለብዙ ዓመታት ሲኖር ከነበረበት ቦታ ኦሮሞዎች እየገፉትና እያጠፉት እንዲሁም የክርስትና ሐይማኖቱ ላይ ያደረሱበት ጉዳት እጅግ ከፍተኛ እንደነበር በበርካታ መጽሀፍት ተጽፏል። የጉራጌ ህዝብ እንደ ትግራዋይና አማራ ህዝብ ስረ-መሠረቱ ሴማዊ የሆነና ቋንቋውም ከሴማዊ ቋንቋዎች ከግዕዝ፣ ከትግርኛና አማርኛ ጋር በእጅጉ የተገናኘ እንደሆነ የስነ-ልሳን ምሁራን በጥናትና ምርምር ጽሁፎቻቸው አመልክተዋል።

የጉራጌ ህዝብ በማንኛውም መስፈርት ሲለካ በቋንቋው፣ በማንነቱ፣ በአመጣጡ፣ በባህሉ፣ በአመጋገቡና በአጠቃላይ ስነ-ልቡናዊ አመለካከቱ ከኦሮሞዎች ጋር መስተጋብር የለውም። ሆኖም እነ ርስቱ ይርዳው ስልጣን ላይ ለመቆየት ከአብይ አህመድ ጋር በመዳራት ዘላቂውን የጉራጌ ህዝብ ጥቅም አሳልፈው በመስጠት ለባርነት እየዳረጉት ይገኛል። ይህንን አስመልክቶ ታዋቂው ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ አቶ መንግሥቱ ለማ “የአባቶች ጨዋታ” በሚል ርዕስ በ1959 ዓ.ም. ባሳታሙት መጽሀፍ ላይ አጼ ዮሐንስ የጉራጌ ህዝብ ላይ 1870ዎቹ ላይ በኦሮሞዎች ይደርስበት የነበረውን ጭፍጨፋ ለማስቆም ያደረጉትን ጥረት ለግብዛቤ እንዲረዳ አቅርበንላችኋል።