በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ የነበረው የሆቴሎች ገበያ መነቃቃት እያሳየ ነው

በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ የነበረው የሆቴሎች ገበያ መነቃቃት እያሳየ ነው

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪ መሠረት ዳያስፖራዎች ወደ አገር ቤት ሲመጡ፣ በተለይ በአገልግሎት ዘርፉ ላይ መነቃቃት እንደሚፈጠር ሆቴሎች ተስፋ አድርገው ነበር። ከእንግዶቹ መምጣት ጋር ተያይዞም በአዲስ አበባና በመላ አገሪቱ የሚገኙ ሆቴሎች፣ በአገልግሎት ዋጋቸው ላይ የ30 በመቶ ቅናሽ በማድረግና አዳዲስ ሁነቶችን በማዘጋጀት ጎብኝዎቻቸው ለመሳብ መሞከራቸውን ይገልጻሉ።