ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ለህዝባቸው ሰላም፣ ትብብር፣ አብሮ መኖርና ልማት ሊሰሩ የሚገባቸው ጊዜ አሁን መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።
–
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ባወጡት መግለጫ፥ ግድቡ ለሀገራቱ ህዝቦች ሰላማዊነት፣ ትብብር፣ አብሮ መኖርና የመልማት እድልን ይዞ የመጣ መሆኑን አስታውቀዋል።
–
የናይል ወንዝ በአጠቃላይ፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በተለይ ለሶስቱ ሀገራት የሰላም፣ የትብብርና የልማት ዓላማ መሳካት ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል።
–