መንግስት ለውጡን የህዝብን ሰላም ከመጠበቅና ሕግና ሥርዓት ከማስያዝ ጋር ማዋሃድ አቅቶታል እየተባለ ቅሬታ ይሰማበታል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አስተያየት

SHEGER FM 102.1 RADIO

ኢትዮጵያ የአስተዳደር ሥርዓት አፈፃፀሟን ለማስተካከል ለውጥ ከጀመረች ሰባት ወራት አለፉ፡፡ በእነዚህ ወራት የሃገሪቱን ፖለቲካዊና ምጣኔ ሐብታዊ እድገት የሚያጎለብቱ ብዙ ተስፋ ሰጪ፣ አነቃቂና ፈጣን የሚባሉ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡

በሌላ በኩል የርስ በርስ ግጭቶች የህዝቡን አኗኗር የማመሳቀላቸው ነገር የቀን ተቀን ወሬ ሆኗል፡፡ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች አንዱ በሌላው ላይ እየተነሳ የሰው ሕይወት ያጠፋል፣ ንብረት ይወድማል፣ ነዋሪዎች ይፈናቀላሉ፡፡

ሕግ፤ በጉልበተኞች እጅ ሆኖ የፈለገውን ርምጃ ሲወሰድ መንግስት ለውጡን የህዝብን ሰላም ከመጠበቅና ሕግና ሥርዓት ከማስያዝ ጋር ማዋሃድ አቅቶታል እየተባለ ቅሬታ ይሰማበታል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ምሁራን ምን ይላሉ ? ለዛሬው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን አስተያየት ይዘናል፡፡ እንዲያዳምጡ ጋብዘናል…