ከጄሶ የተሰሩ ህገወጥ መድሃኒቶች በኢትዮጵያ እየተሰራጩ እንደሆነ ተነገረ፡፡

SHEGER FM 102.1 RADIO

ከጄሶ የተሰሩ ህገወጥ መድሃኒቶች በኢትዮጵያ እየተሰራጩ እንደሆነ ተነገረ፡፡

የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን በሀገሪቱ ካለፉት 2 እና 3 አመታት ወዲህ የህገወጥ መድሃኒቶች ዝውውር እየጨመረ መምጣቱን ተናግሯል፡፡

ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ከሚወሰዱና ከሚሸጡ መድሃኒቶች መካከል ለስንፈተ ወሲብ የሚያገለግለው ቬጎ የተባለው መድሃኒት ይገኝበታል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልመዘገባቸውና ደህንነትና ፈዋሽነታቸውም ያልተረጋገጡ መድሃኒቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት ከጎረቤት ሀገራት መሆኑንም ሰምተናል፡፡

የሚሰራጩት ህገ-ወጥ መድሃኒቶችም ባለስልጣኑ ፈቃድ ከሰጣቸው ጋር ፍጹም ተመሳሳይ መሆናቸው ለቁጥጥር አስቸጋሪ አድርጎታል ተብሏል፡፡

ዲላ፣ ሆሳዕና፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ህገ-ወጥ መድሃኒቶቹ በብዛት ይዘዋወሩባቸዋል ከተባሉት ከተሞች ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ችግሩን ለማስወገድና ለሕብረተረሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚዲያ ፎረም አዘጋጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US