የዘማሪ ደረጀ ከበደ ክርስቲያናዊ መልዕክትና የሶፍያ ሽባባው “ብልጽግናዊ” ለቅሶ

የዘማሪ ደረጀ ከበደ ክርስቲያናዊ መልዕክትና የሶፍያ ሽባባው “ብልጽግናዊ” ለቅሶ

ዘማሪ ዶ/ር ደረጀ ከበደ በአማራ ህዝብ ላይ አብይ አህመድ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ ያስተላለፈው ወቅታዊና በማስረጃ የተደገፈ መልዕክት ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በስፋት ተሰታጭቶ የብዙ ሰዎች መነጋገሪያ ሆኗል። ዘማሪ ደረጀ ያቀበው መልዕክት የአማራ መሬት ለትህነግ ክፍት ተደርጎለት ከራያ አንስቶ እስከ ደብረ ብርሃን ሊደርስ የቻለበትን ምክንያት በዝርዝር አስቀምጧል። ሆኖም እርጉዝ የአማራ ሴቶች ሆዳቸው በጩቤ እየተሰነጠቀና አንገታቸው ታርደው ሲጣሉ፣ ለአቅመ ሔዋል ያልደረሱ ልጃገረዶች ሲደፈሩ፣ ወንዶች ሲሰለቡ፣ ሲታረዱ፣ ቤታቸውና እህላቸው ሲቃጠልባቸው እንዲሁም ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀልና የዘር ማጥፋት ሲደርስባቸው አንድም ቀን ትንፍሽ ያላሉ አብይ ተነካብን ብለው በመወራጨት ላይ ናቸው። አንዳንድ ዘማሪያንም ማስፈራት ጀምረዋል ሌሎችም እየተራገሙ ነው። እነዚህ ግለሰቦች አምላካቸው እየሱስ ክርስቶስ ሳይሆን አብይ አህመድ መሆኑን በስራቸው እያረጋገጡ ነው።

ከነዚህም አንዷ የአብይ ውሻ ሶፍያ ሽባባው ስትሆን አማራው ላይ በኦሮሙማ የሚደርሰው የዘር ማጥፋት ለምን ተነሳ ብላ የአዞ እንባ እያፈሰሰች ዘማሪ ደረጀን ለመውቀስ የምትሄድበት ርቀት እጅግ ያሳዝናል ያስተዛዝባልም። ሶፊያ ሽባባው ክርስትና ሐይማኖትን በአፍጢሙ ፈጥፍጣ፣  መጽሀፍ ቅዱስን በእግሯ ረግጣ አብይን አምላኳ በማድረግ ለተበደለና ለተጠቃ መጮህን ስታወግዝና ስታጣጥል መመልከት አብይ እህመድ የብዙዎችን አይምሮ እንደመረዘ ማረጋገጫ ነው። ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ትግስት ሚዲያ ላይ የተላለፈውን ወቅታዊ መልዕክት አቅርበንላችኋል።