ጋዜጠኛ መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ ታሥሯል

መታሰሩን በፌስቡክ ገጿ ያሳወቀችን ባለቤቱ ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ተስፋው ናት። የብርሃኑን መታሰር ተከትሎ የታሰረው በዚህና በዚያ ነው። ዐቢይ አሕመድ ነው ያሳሰረው፣ ብርሃኑ ነጋ ነው ያስቀፈደደው ብላብላ ብሎ የሌለ ዘገባ ለመሥራት መጣደፍም ተገቢ አይደለም። ነገርን ከሥሩ፣ ውኃን ከጥሩ መቅዳት መልካም ነው። ወደቀ ሲባል ተሰበረ ለማለት መጣደፍም ሸጋ አይደለም። አዎ ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለያሬድ ታስሯል የታሰረው ግን በፖለቲካ አቋሙና አመለካከቱ አይደለም። የታሠረው በእኛው ቤት ጉድ ነው። አበቃ።

… ነገሩ እንዲህ ነው። የሆነ ወቅት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና በሰንበት ትምህርት ቤቱ መካከል ግጭት ይፈጠራል። ግጭቱ እየጋመ ሄዱ ወደ ሁከት ይቀየራል። በዚህን ጊዜ አለቃው ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ወስደው አቤት ይላሉ። ፖሊስም የሰንበት ተማሪዎችን ያስራል። በዚህ መሃል ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ዘገባ ይሠራል። ለለለቃውም ዕድል አመቻችቶ ሚድያ ላይ ያቀርባቸዋል። ቆይቶ ግን በመሪጌታ ዘገባ ያልተደሰቱት አለቃው “ስሜ ጠፍቷል” ብለው ለፌደራል ፖሊስ ይከሱታል። ፌደራል ፖሊስ ዘንድ ሄዶ ስንፈልግህ ትመጣለህ ብለው ከዚህ በፊት እንደመለሱት ይታወቃል። ያ ክስ ነው አሁን የተንቀሳቀሰው።

…በቀጨኔ ደብረሰላም መድኃኔዓለም አስተዳደርና በሰንበት ትምህርት ቤቱ መካከል ዕርቅ ወርዷል። ረዳት ፕሮፌሰር ባዬ እና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በግል ጣልቃ ገብተው በደብሩ እርቅ ወርዶ ሁላቸውም ተስማምተዋል። አሁን ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ሰላም ወርዷል።

…ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በቀጨኔ መድኃኔዓለም በምርግትና አገልግሏል። ያደገበት ደብር ነው። አሁን የሚያስፈልገው አባትና ልጅ አለቃ ክቡር መላከ ሰላም ስዩም ወ/ገብርኤልንና መሪጌታ ብርሃኑን አቀራርቦ ማስታረቅ፣ ይቅር ማባባል እንጂ ጉዳዩን በግድ ጠምዝዞ ወደ ሌላ መንገድ መውሰድ አያስፈልግም። ላም ባልዋለበትማ ኩበት አታስለቅሙን እንጂ።

…ክቡር አባታችን መልአከ ሰላም ስዩም ወልደ ገብርኤል ሆይ ነገሩን ይተዉት። ለማንም አይጠቅምም። ይቅርም ይበሉት። ታረቁ። በመካከላችሁ ማንም አይግባ። በአንድ መቅደስ የምታገለግሉ አባትና ልጅ ናችሁ። እንደ ጦስ ዶሮ ከጀርባዎ ሆኖ ሌላ ኃይል ሊጠቀምብዎ ካልፈለገ በቀር ነገሩ ከዚህ የሚያደርስም አይደለም። አባታችን ይታረቁ። ይቅርም ተባባሉ።

…እና ምን ለማለት ፈሊጌ ኖ። ነጭ ነጯን ስንነጋገር መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ጥሶ አይደለም የታሰረው። በብሬ እስር በዘመቻ ላይ በረሃ ወርዶ የሚንከራተተው አቢቹም፣ የት እንዳሉ የማላቃቸው ዶፍቶር ብርሃኑ ነጋም የሉበትም። እስከአሁን እኔ ያለኝ መረጃ ይሄው ነው።