በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኘው: በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተመራውና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ብ/ክ/መ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንድአርጋቸው እና ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች የሚገኙበት ልዑክ ከሰዓት በኃላ ላይ ወደ ላሊ-በላ በማቅናት የላሊ-በላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ጥበቃና ጥገና የሚገኝበትን ሁኔታ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል::
በጉብኝቱ ላይ በድንገት ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚንስትሩ: ላሊ-በላን የሚያክል ድንቅ የዓለምና የአፍሪካ ቅርስ: ለእኛ ደግሞ ከዚያም በላይ መኩሪያችን ስለሆነ ደግመን መገንባት ባንችል እንኳ መጠበቅ ግን ግዴታችን ነው” ብለዋል::