ተራኪ፡ የሩጫ ዘመን የወለደው የመጻሕፍት ትረካ መተግበሪያ

ጓደኛሞቹ ናሆም ጸጋዬ እና አቤል እንግዳ ተራኪ የተባለ የመጻሕፍት ትረካ መተግበሪያ ፈጥረዋል። ተራኪ ወደ 9 ሺህ ገደማ ተጠቃሚዎች በስልካቸው ጭነውታል። በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በእንግሊዘኛ የተጻፉ መጻሕፍት ትረካዎች አሉት። ልብ ወለድ፣ እውነተኛ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ፖለቲካ፣ የልጆች ተረት እና ሌሎችም መጻሕፍት ይዟል።…