ሰበር ዜና – ጠ/ሚ አብይ አህመድ ሰራዊቱ ድል እያስመዘገበ በመገስገስ ላይ እንደሚገኝ ከግንባር ሆነው መግለጫ ሰጡ

የምንፈልገው እኛ ሞተን ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ማድረግ ነው፤ የኢትዮጵያ ነጻነት አስኪረጋገጥ ወደ ኋላ ማለት የለም። ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ

ውጤቱ እጅግ በጣም ጥሩ ነው ። ከጀርባ የምታዩት ጠላት በሙሉ የያዘው ተራራ ነበር አሁን አስለቅቀናል። ጠላት ከኛ ጋር የሚፎካከር ቁመና የለውም ። ካሳጊታን ይዘናል፤ ጭፍራ እና ቡርቃን ዛሬ እንይዛለን፡፡ ነገም ይቀጥላል ትልልቅ ድሎች አሉ ። ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግንባር ባስተላለፉት መልዕክት የወገን ጦር በከፍተኛ ሞራልና ወኔ እየተዋጋ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ጠላት የያዛቸውን ቦታዎች እያስለቀቀ መሆኑን ጠቅሰው፥ ጠላት የወገንን ጦር የመገዳደር አቅም እንደሌለውም ነው የገለጹት። አሁን ላይ የወገን ጦር ደርሳጊታን – ካሳጊታን መቆጣጠሩን ጠቁመው፥ ቡርቃ እና ጭፍራን ዛሬ እንደሚቆጣጠርም አስታውቀዋል።