ህወሓትን በሚደግፉ ተመራቂ ምሁራን ላይ ዲግሪዎችን መንጠቅን ሊያካትቱ የሚችሉ እርምጃዎች እወስዳለሁ – አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ሀገር አፍራሽ የሆነውን የህወሓት ቡድንን የሚደግፉ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ምሁራን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ካልሆነ ግን ዲግሪያቸውን እስከመንጠቅ የሚደርስ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።  ዩኒቨርሲቲው አሸባሪው ህወሓት በንፁሃን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ እና ሀገር ለማፍረስ የሚያደርገውን ሴራ አውግዟል።

Addis Ababa University (AAU) has issued warning against graduate academics to refrain from acts of supporting the TPLF. The University said the measures may extend up to revoking academic degrees of individuals who are found to be supporting the TPLF. The University also “condemned the TPLF’s atrocities against innocent people and its conspiracy to destroy the country,” according to state broadcaster EBC.

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች አሸባሪውን ህወሓት እና ደጋፊዎቹን በማውገዝ ከኢትዮጵያ ጎን መቆማቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በተቃራኒው ግን ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ለሀገር የዋለውን ውለታ በመካድ ከሀገር አፍራሽ ሽብርተኞች ጋር የተባበሩ ጥቂት ግለሰቦች መኖራቸውን ጠቅሷል።

እነዚህ ከሃዲዎች ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ዲግሪያቸውን እስከመንጠቅ የሚደርስ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስገንዝቧል። በሌላ በኩል ምዕራባዊያን ኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድሩትን ያልተገባ ጫና እንዲያቆሙም ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።  ዩኒቨርሲቲው የጀመረውን ሀገርን የማዳን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማሳወቅ፣ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ እና የኅልውና ዘመቻውን በተመለከተ 8 ነጥቦችን የያዘ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። EBC