አዲሱ የሱማሌ ክልል መስተዳድር የለውጥ ሂደቱን በሚያደናቅፉ ሃይሎች ላይ እርሚጃ በመውሰድ የህግ የበላይነትን ማስጠበቅ ይኖርበታል!

አዲሱ የሱማሌ ክልል መስተዳድር የለውጥ ሂደቱን በሚያደናቅፉ ሃይሎች ላይ እርሚጃ በመውሰድ የህግ የበላይነትን ማስጠበቅ ይኖርበታል!

“ለብዙ ዓመታት በአማራው ላይ ስር የሰደዱ አሉታዊ ስብከቶች ስለነበሩ፤ የመጀመሪያ ልዑካን ቡድናችንን በቅርቡ ወደ አማራ ክልል እንዲሄድ እናደርጋለን” ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት

ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በክልል ደረጃ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን እስከ ቀበሌ ድረስ የሚሰራ ነው። በቀበሌ፣ በወረዳም ሆነ በዞን የአስተዳደር ቦታወች ላይ የሚሾሙት ህጉን ተከትሎ ህዝቡ በመረጣቸው በራሳቸው ሰዎች መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ግን ከሌላ ቦታ አምጥቶ የምጫንባቸው ከሆነ አግባብነት የለውም ምክንያቱም ወረዳ፤ ዞንም ሆነ የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በራሳቸው ሰዎች መመራት አለባቸው የሚባለው በዋናነት የራስን በራስ የማስተዳደርን መብት ለማስከበር ሲሆን ሌላው ደግሞ ለወረዳው፤ ለዞኑም ሆነ ለከተማ አስተዳደሩ እድገትና ለሕዝቡ ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ የሚችለው ከሌላ አካባቢ ከመጣ ሰው ይልቅ የወረዳው፤ የዞኑ ወይም የከተማ አስተዳደሩ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ላለፉት አስር አመታት በቀድሞው የክልሉ አስተዳደር በዞን፤ በወረዳና በከተማ አስተዳደር ላይ በኃላፊነት የሚሾሙት ሰዎች ከዚህ በላይ ከተገለጸው ውጪ በሆነ መልኩ በቀጥታ በክልሉ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ምደባ ይከናወን የነበረ በመሆኑ ህዝቡን ለተቃውሞ የዳረገ፤ በክልሉ ውስጥ ባሉ ዞንና የወረዳ አስተዳደሮች ላይ ለተከሰተው መጠነ ሰፊ የሆነ ሙስናና ብልሹ አስተዳደር መንስኤ በመሆኑ አዲሱ የክልሉ አስተዳደር ስህተቱን ለማረም እንዲቻል በዞን፤ በወረዳና በከተማ አስተዳደር ላይ በኃላፊነት የሚመደቡትን ኃላፊዎች ከአካባቢው ከተውጣጡ ተወላጆች ያዋቀረ ቢሆንም በአንዳንድ ወረዳዎች ላይ ከጎሳ ተዋጽኦና ከስልጣን ክፍፍሉ ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች ሳቢያ የፀረ ለውጥ የሆኑ ሃይሎች ህዝቡን ለተቃውሞና ለጎሳ ግጭት መቀስቀሻ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያህል በትናንትናው እለት በሊበን ዞን በፊልቱ የወረዳ መስተዳድር ም/ቤት ላይ በታጠቁ ሃይሎች በተቀነባበረው ሴራ ለደረሰው የሰው ህይወት ህልፈትና ጉዳት ከጀርባ ሆነው የመሩት የፀረ ለውጥ ሃይሉ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ስለዚህ የክልሉ መስተዳደር ከክልሉ መስተዳድር በታች ባሉት የዞን፤ የወረዳና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ላይ በተከናወነው የሥራ ኃላፊዎች ምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታዎች በተነሱባቸው ወረዳዎች ላይ ለህዝቡ ተገቢውን ምላሽ መስጠትና እንዲሁም የጎሳ ግጭት በሚቀሰቅሱ የፀረ ለውጥ ሃይሎች እርሚጃ በመውሰድ የህግ የበላይነትን ማስጠበቅ ይኖርበታል፡፡

“ለብዙ ዓመታት በአማራው ላይ ስር የሰደዱ አሉታዊ ስብከቶች ስለነበሩ፤ የመጀመሪያ ልዑካን ቡድናችንን በቅርቡ ወደ አማራ ክልል እንዲሄድ እናደርጋለን” ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት

ሃገር በተማሩ ሰዎችና ልምድ ባላቸው ፖልቲከኞች ከተመራች መለወጧ አይቀርም። ምስራቅ ኢትዮጵያይቱ ሶማሊ ክልል ለዘመናት የተበደለችው ሰው አጥታ አልነበረም (ከየትኛውም ክልል የማያንሱ ያውም በአውሮፓ ታዋቂ ዪኒቨርስቲዎች የተማሩ) ከክልሉ ኣልፈው ለኢትዮጵያ አስተዋስጾ ማበርከት የሚችሉ እንቁ ልጆች ነበሯት/አሏት። ነገር ግን የሶማሊ ክልል ሙህራኖች እጣ ፈንታቸው ሶስት ነበር። 1, እስር ቤትን ቤታቸው ማድርግ፣ 2, ስደት፣ 3, መስሎ ማደር። ከክልሉ ኣቅም ያለው ሰው ወዴ ፖለቲካውና ሃግራዊ ጉዳይ ኣካባቢ እንዳይዟዟር ከክልል እስከ ፌድራል ድረስ ባልተጻፈ ህግ ተከልክሎ ነበር። ዛሬ ግን ሁኔታዎች እየተቀየሩ ይመስላል። እንዴ ኣብዱልዋሳ ያሉት የክልሉ ሙህራን ሚኒስትር ዴታ ሁነዋል። በውጩ አለም ስፊ ልምድ ያካበቱት የክልሉ ተዎላጅ ሙህርና ፖልቲከኛው ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር የክልሉ ፕሬዝዳንት ሁነው ከክልሉ ኣልፈው ለሀገሪቱ ተስፋ እየሆኑ ነው። አሁን ደግሞ ክልሉ ከሌሎች እህት ክልሎች ጋር ለሚኖረው ወዳጅነት ቅድሚያ ስጥተው ሊስሩ ምሆኑን እየሰማን ነው። ይበል የሚያስኝ ነው።