የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የሶስትዮሽ ውይይት ለቀጠናው ሰላም መጠናከር እንደመልካም ጅማሮ ተወስዷል

ለበርካታ አስርት ዓመታት በፖለቲካ ምስቅልቅል ውስጥ የከረመው የምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች እየታዩበት ስለመሆኑ ብዙዎች ይመስክራሉ። በተለይም የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እያደረጉት ያለው የሦስትዮሽ ውይይት ለቀጠናው ሰላም መጠናከር እንደመልካም ጅማሮ ተወስዷል።