ከ40 በላይ የባልደራስ አባላትና ደጋፊዎች በጅምላ ታፍሰው ታስረዋል።

የእነ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የሄዱ ከ40 በላይ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባላትና ደጋፊዎች በአፈሳ ታስረዋል።
አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ ተከትሎ ችሎት አልተሰየሙም ነበር። ይህንን የሰሙ ታዳሚዎች እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው ወጥተዋል። ከዚያም የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታግተው ውለዋል። ምሽት አንድ ሰዓት ገደማ ደግሞ ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ታስረዋል። ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባሉ ተብሏል።