በምሥራቅ ወለጋና ሆሮጉድሩ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጽመው ጥቃት ብሄር ተኮር ወደሆነ የርስበርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋና ሆሮጉድሩ ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጽመው ጥቃት ብሄር ተኮር ወደሆነ የርስበርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል ሲል ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስጠንቅቋል። በምሥራቅ ወለጋ ዞን በኪራሙ ወረዳ ሐሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተከታታይ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን ተከትሎ፣ ኢመደበኛ አደረጃጀት ያላቸው የአካባቢውና የአጎራባች ክልል ነዋሪዎች ሌሎች በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን እንደገደሉ ከአስተዳደር አካላት መስማቱን ኮሚሽኑ ጠቅሷል። በሆሮ ጉድሩ ወረዳ ኡሙሩ ወረዳም፣ ከነሐሴ 12 ጀምሮ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ጦር መሳሪያ የታጠቁ ነዋሪዎች በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን እንደገደሉ ኮሚሽኑ ገልጧል። በጥቃቶቹ የኦሮሞና አማራ ብሄር ተወላጆች እንደሞቱ የገለጠው ኮሚሽኑ፣ አካባቢው ብሄር ተኮር የርስበርስ ግጭት ስጋት አንዣቦበታል ያለው ከሚሽኑ፣ መንግሥት በአካባቢው በአፋጣኝ ቋሚ ጸጥታ ኃይል እንዲያሠፍር አሳስቧል።በምስራቅ ወለጋ ያለውን ግጭት በመሸሽ ከ43 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

በምስራቅ ወለጋ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ግጭት በመሸሽ በአጠቃላይ 43,139 ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ የዞኑ የአስተዳደርና የፀጥታ አካላት አስታውዋል፡፡
ነዋሪዎቹ የተፈናቀሉት በምስራቅ ወለጋ በሚገኙ ,ሊሙ ፣ ጉደያ ቢላ ፣ ኪረሙ ፣ ሌቃ ዱለቻ ፣ በዲጋ ፣ እና ቸከሆሮ በሚባሉ 5 ወረዳዎች እና ጉድሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ መሆናቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) ከዞኑ አስተዳዳሪዎች መስማቱን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ወደ እነዚህ አከባቢዎች የሚያደርሱ መንገዶች አሁንም ዝግ በመሆናቸውና በአከባቢው ያለው ውጥረት አሁንም ባለመርገቡ ምክንያት ሰዎች መሰረታዊ አቅርቦቶችንና ሕክምና ለማግኘት ጭምር በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ ኢሰመኮ ነው የገለጸው፡፡

ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንዳሉት የፀጥታ አስከባሪዎች አንድን አካባቢን ለቅቀው ሲሄዱ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ዋነኛው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በቂ የፀጥታ ኃይሎች በተለይ ለግጭትና ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ በቋሚነት የጸጥታ ሃይሎችን መመደብ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡