ተፈናቅለው በደሴ ተጨናንቀው የሚገኙ ሰዎች በሕወሓት እንደተዘረፉና ሴቶችም በሕወሓት ታጣቂዎች እንደተደፈሩ ተናግረዋል።

ዛሬ ሮይተርስ በድረገፁ ከደሴ ከተማ የተሰራ ሰፋ ያለ ዘገባ አስነብቧል።

Ethiopian families fleeing fighting describe hunger, rape in Amhara

Another woman at the camps told Reuters that she had been raped by an armed man speaking Tigrinya, the language of Tigray, in an area of Amhara under Tigrayan control. Saada, 28, told Reuters she had been attacked in her house in Mersa, 80 km north of Dessie, by the armed man in plain clothes. She did not recall the exact date but said it was around the end of August.”He said to me ‘We left our houses both to kill and to die. I am from the jungle so, I have all the right to do whatever I want. I can even kill you’ and he raised his gun to me and threatened to kill me,” she said. “Then he raped me.”

በዚሁ ዘገባ አንዲት ሀብታም አከለ የምትባል እናት በምግብ እጥረት ምክንያት ልጇን እንዳጣች ተናግራለች።

ሀብታም የ3 ዓመት ህፃን ልጇን በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ባለፈው ወር ነው ያጣችው ወደ ደቡብ የአማራ ክልል ክፍል ከመሸሻቸው በፊት።

ሀብታም ፥ ዶክተሮች ልጇ በምግብ እጥረት በጣም እንደተጎዳች በዚህም ምክንያት ልጇን ሊረዷት እንዳልቻሉ እንደነገሯት ተናግራለች። ዶክተሮቹ መድሃኒት ቢሰጧትም ትንሿ የሀብታም ልጅ በትክክል ከሳምንት በኃላ ህየወቷ አልፏል።

ሀብታም የሰሜኑን ጦርነት ሽሽት ወደ ደሴ ከተሰደዱ በሺዎች ከሚቆጠሩ የአማራ ቤተሰቦች አንዷ እንደሆነች ሮይተርስ ፅፏል።

በደሴ ተፈናቃዮች በትምህርት መማሪያ ክፍል ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ በረድፍ ነው የሚተኙት ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ያገረሸው ግጭት ደግሞ ይህን ያባብሰዋል ተብሎ ይሰጋል።

ሀብታም በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች አነስተኛ ምግብ እንዳለ እንዲሁም የትግራይ ኃይሎች በአካባቢው ከሚገኙ ፋርማሲዎች ያለውን አነስተኛ መድኃኒቶችን እንደዘረፉ ተናግራለች።

የህወሓቱ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ግን ይህንን ክስ እንደማይቀበሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል፤ ይልቁንም ሃብታም ትኖር በነበረበት አካባቢ በጄኔሬተር ያለውን ውሃ እጥረት ለመቅረፍ መስራታቸውን ገልፀዋል።

ሌላ በካምፕ ውስጥ የምትገኝ እና ሮይተርስ ያነጋገራት አንዲት ሴት በታጠቀ የትግራይ ኃይል መደፈሯን ገልፃለች። ይህ የተፈፀመባት በትግራይ ኃይሎች ስር ባለ የአማራ ክልል አካባቢ ነው።

ስሟ ሰዓዳ ይባላል እድሜዋ 26 ሲሆን ከደሴ 80 KM በምትገኘው በመርሳ ከተማ ቤቷ ውስጥ እያለች ነው ይህ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባት።

ሰዓዳ ትክክለኛውን ቀን ባታስታውሰው። ድርጊቱ ነሐሴ መጨረሻ አካባቢ መፈፀሙን ተናግራለች።

ሰዓዳ እንደደፈራት የገለፀችው የትግራይ ኃይል ፥ ” እኛ ቤታችንን ጥለን የወጣነው ለመግደልም ለመሞትም ነው። እኔ ከጫካ ነው የመጣሁት የፈለኩትን የማድረግ ሙሉ መብት አለኝ፤ ልግድልሽም ሁሉ እችላለሁ” ብሎ ጠመንጃውን ከፍ አድርጎ ካስፈራራት በኃላ እንደደፈራት ለሮይተርስ ተናግራለች።

ሰዓዳ ሮይተርስ ሙሉ ስሟን እንዳይጠቀም የጠየቀች ሲሆን ከተደፈረች በኃላ ለህክምና ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መሄዷንም የሚያሳይ ካርድ አሳይታለች።

የደሴ ሆስፒታል ሜዲከል ዳይሬክተር አቶ ልዑል መስፍን ስለሲቪል ጉዳት፣ ስለ አስገድዶ መድፈር ወይም ስለ ግለሰብ ጉዳይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል ፤ ለዚህ ምክንያታቸው የውጭ ጋዜጠኞችን ስለማያምኑ መሆኑ እንደገለፁ ሮይተርስ ፅፏል።

የህወሓቱ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ስለፆታዊ ጥቃቱ ተጠይቀው ክስተቱ ለመረመር እንደሚችል ነገር ግን የአንድ ሰው ድርጊት የመላው የትግራይ ኃይሎችን ሊያካትት አይገባም የሚል መልስ ለሮይተርስ ሰጥተዋል።

ሙሉውን ያንብቡ : https://www.reuters.com/world/africa/ethiopian-families-fleeing-fighting-describe-hunger-rape-amhara-2021-10-18/