በአዲስ አበባ ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ታፍሰው በጦላይ የቆዩ ወጣቶች ከእስር ተለቀቁ!!

 

በአዲስ አበባ ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ታፍሰው / በቁጥጥር ስር ውለው በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 1 ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።

ከአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ ታፍሰው ወደ ጦላይ ወታደራዊ ካንፕ የተጋዙትን 1174 ወጣቶች “ሰላም የሁላችን ስለሆነች እንጠብቃት” የሚል ትሸርት አልብሰው ስልጠናው ጥሩ ነበር ታርመናል በመምጣታችን ደስተኛ ነን የሚል ፕሮፓጋንዳ እየሰሩባቸው ነው ። የሀይለማርያም ኢህአዴግም “አይደገምም” የሚል ትሸርት ያለብስ ነበር ። ለማንኛውም ልጆቹ ከፓርቲ ሚዲያ ውጪ ከተፈቱ በሀላ ነፃና ገለልተኛ ሚዲያ ካገኙ የሆነውን እንዴት እንደተያዙ የት እንደተያዙ ? ጦላይ ምን እንዳጋጠማቸው ይነግሩናል ብዬ ተስፍ አደርጋለው ።

ታፍሰው ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩት 1 ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር መለቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

Image may contain: 2 people, people standing, outdoor and nature