በኦሮሚያ አዲስ መንግሥት ሲመሰረት እነማን ተሾሙ?

አዲስ በተመሠረተው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፕሬዝደንት፣ አቶ አወሉ አብዲ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነዋል። በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ 5 ባለሥልጣናት ተሾመዋል። 32 አባላት ካሉት የአቶ ሽመልስ ካቢኔ አስሩ ሴቶች ናቸው። የኦነግን አንድ አንጃ የሚመሩት አቶ አራርሶ ቢቂላ የኦሮሚያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል…