ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስሩን የጨረሰውን ጋዜጠኛ አለቅም፤ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልቀበልም ብሏል ።

ፍትህ ለጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው
የከፍተኛው ፍ/ቤት የጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን ጉዳይ ከመረመረ በኃላ የማረሚያ ቤት ቆይታውን ከአራት ወር ወደ አንድ ወር እንዲቀነስ አዟል፤ በዚህው ዉሳኔ መሰረት የጌጥዬ ያለው የእስር ቤት ቆይታ ባሳለፍነው ሳምንት ቢጠናቀቅም ጋዜጠኛው ከእስር ቤት ሊለቀቅ አልቻለም፡፡
ፍርድ ቤቱ ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው እንዲፈታ ትዕዛዝ ቢሰጥም ማረሚያ ቤቱ ትዕዛዙን ሊፈፅም አልቻለም፡፡ ዛሬም የፍትህ ያለህ እንላለን፡፡
ከእውነት፣ ከዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና ከፍትሕ ጥያቄዎች ውጭ ምንም የግል አጀንዳ የሌላቸውን ዜጎች ማሰር ነውር ነው፡፡
ይህ አልበቃ ብሎ የሀገሪቱ ፍ/ቤት የወሰነውን ውሳኔ አስፈፃሚው አካላት መፈፀም አለመቻላቸው የፍትህ ስርዓቱን መዝቀጥ አመላካች ነው፡፡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚታዩት ጥሰቶች አስፈፃሚውን አካል ማስጠየቁ አይቀርም፡፡ ፍትህ በሃሰት ለተወነጀሉ ንፁሀን የባልደራስ አመራሮች!!! ፍትህ ለጌጥየ ያለው!!!