ለመቀሌና ለሕወሓት ሀይል ቁልፍና ስትራቴጂክ ከተማ የሆነችው ምላዛት በአፋር ሀይሎች ቁጥጥር ስር ዋለች

በአፋር ክልል በኩል እየገባ በመተንኮስ መግለጫ የሚያወታው ሕወሓትን ለመቅጣት የዘመቱት የአፋር ሚሊሻዎች ድል እንደቀናቸው ከአብዓላ ወረዳ ተሰምቷል ።

የአፋር ክልል ልዩ ሀይልና ሚኒሻዎች በአብአላ በኩል ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ በመግባት 4 የትግራይ ከተማዎችን መቆጣጠራቸው ተነገረ ።

ይህ በኢንዲህ እንዳለ በአሁን ሰአትም ከመቀሌ በ30ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኘውና ለመቀሌና ለሕወሓት ሀይል ቁልፍና እስትራቴጂክ ከተማ የሆነችውን ምላዛት የምትባል ከተማን በአፋር ሀይሎች ቁጥጥር ስር መሆኗ ተረጋግጦል፡፡

ሕወሓት ከቀናት በፊት አፋር ክልል ላይ የሞከረው ትንኮሳ ከሽፎበት ሲባረር የአፋር ክልላዊ መንግስትን የሚወነጅል መግለጫ ማውታቱ ይታወሳል።