ሳምራዊት ፍቅሩ፡ የራይድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ዓለም አቀፍ ሽልማት ተሸለመች

ሳምራዊት ፍቅሩ በሙያዋ ኮምፒውተር ፕሮግራመር ናት። ተቀጥራ በምትሠራበት ወቅት ከደሞዟ 40 ሺህ ብር ያጠራቀመች ሲሆን በዚህም “ራይድ” የጥሪና የአፕልኬሽን የትራንስፖርት አገልግሎትን መስርታለች። ይህ ድርጅት በአሁን ሰዓት ከ37 ሺህ አሽከርካሪዎች ጋር የሥራ አጋርነት ፈጥሯል። በ2013 የበጀት ዓመትም ከ347 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት ግብር አስገብቷል። በዚህ እና በሌሎች ምክንያቶችም ሳምራዊ…