መንግስት ከሕወሓት ጋር በከፊል ድርድር መጀመሩ ምን ያሕል አዋጪ ነው ? ( ምንሊክ ሳልሳዊ )

መንግስት በከፊል ድርድር መጀመሩ ምን ያሕል አዋጪ ነው ? ሕወሓት ምን ያሕል ለፖለቲካ ታማኝ ነው ? ድርድር ለሕወሓት ጊዜ መግዣና የማዘናጊያ ስልት ነው ! ( ምንሊክ ሳልሳዊ )


May be an image of 2 peopleወደ ዕውነታው ስንመጣ ፦ ለሰላም ሲባል የማይከፈል መስዕዋትነት የለም። ጦርነት ለማቆምም መደራደር፣ በከፊል ለትግራይ የተለቀቁ መብራትና ኢንተርኔትን በሙሉ ለመልቀቅ መደራደር በጥቅሉ ድርድር በተለይ ከሕወሓት ጋር ማድረጉ ምን ያሕል አዋጪ ነው ? እንደ ሕዝብ መንግስትን ለመጠየቅ እንገደዳለን። ግፋ ዝመት ታጠቅ ተኩስ በለው ሲሉ የነበሩ ከፍተኛ ሚኒስትሮች ሰሞኑን ስለ ሰላምና ድርድር በየማሕበራዊ ድረገፆች ሲጽፉ እያስተዋልን ነው፤ ሰላምን የሚጠላ የለም፤ ከሕወሓት ተፈጥሮ አንጻር ግን መመዘን ግድ ይላል ።

ሕወሓት በተፈጥሮው በድርድር ላይ ያለው አቋምም ይሁን ድርድርን ተከትሎ በተግባራዊነቱ ላይ ያለው አሻጥር የሚታወቅና በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። ሕወሓት ለሕዝብ በሚያደሉ ፖለቲካዎች ላይ ታማኝ አይደለም። ለጊዜው ለማዘናጊያና ጊዜ ለመግዣ የሚጠቀምበት ስልት ነው።

ሕወሓትን የሚያውቁ ሰዎች የምንስማማበትና ሕወሓት በጉያው ሆነውም የነበሩ ተጎጂዎች እንደሚመሰክሩት የሕወሓትን ታሪክ ወደ ኋላ ዞር ብሎ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ ድርጅቱ በታሪኩ ይህ ነው የሚባል በሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሠረተ የድርድር ታሪክ የለውም፡፡ ሕወሓት በድርድር የፈታው ችግር ኖሮ አያውቅም፡፡ ድርጅቱ ወደ በረሃ ከወረደ 47 ዓመታት አለፈዋል፡፡ እስከዛሬ ግን በድርድር የፈታው ምንም ዓይነት ችግር የለም፡፡ በረሃ እያሉ ኢዲኅ፣ ጥራናፌት፣ ኢሕአፓ ወዘተ… ከሚባሉ ድርጁቶች ጋር ተገዳድለው ተላልቀው ነው የጨረሱት፡፡ ከዚያም ቀጥሎ የኦነግ ኀይል ጋር፤ ከሻዕቢያ ጋር ልዩነቶቻቸውን የፈቱት በመሣሪያ ኀይል ነው፡፡ ብዙ ታሪኮችን ወደ ኋላ ብናይ ሕወሓት በመነጋገር፣ በመደራደርና በመወያየት የፈታው ችግር የለም፡፡ ተፈጥሮውም ችግርን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚያስችል አይደለም፡፡ ሕወሓት ድርድርን የሚያየው አንድም እንደ ጊዜ መግዣ፤ ሁለትም ሙሉ በሙሉ ለማሸነፍ ነው፡፡ ሰጥቶ መቀበል የሚባል ነገር የማያውቅ ፀረ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

የቀደሞ የመቀሌ ከንቲባ ሰሞኑን እንደተናገሩት በታሪክ እንደ ሰው በግለሰብ ደረጃ የሚፈጠሩ ልዩነቶችም ካሉ እስከ መጨረሻው መሳደድ እንጂ ተጣልተው የታረቁ የድርጅቱ የበላይ አመራሮች የሉም፡፡ እንትና እና እንትና በትግል ላይ ተጣሉ፤ ከዚያም በድርድር ታረቁ ሲባል ሰምቼ አላውቅም፡፡ ግለሰቦች የዕድሜ ልክ ጠላት ሲሆኑ ነው የምናየው፡፡ ሕወሓት ልዩነትን በድርድር ይፈታል የሚል እምነት እና ተስፋ የለኝም፡፡ ይህ ልምድ ቢኖር እንደ ሕዝብ እኛ እንጠቀማለን፡፡ ልዩነቶች በጠረጴዛ ዙሪያ ቢመጡ እውነት ጠርቶ እየወጣ ለሚዳኘውም እውነት እየወጣለት የተደናገረው ሕዝብም እውነት እየተገለጠለት ከመደናገር ነጻ ሆኖ ማንን መደገፍ እንዳለበት የሚያውቅበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር፡፡ ብለዋል ።

ሕወሓትን በድርድር አደብ አሲዘዋለው ማለት ድንጋይ ላይ ውHእ ማፍሰስ ነው ። ሕወሓት በውስጥም በውጪም ጉዳዩ ላይ በድርድር የፈታው አንድም ችግር የለም፤ ሕወሓት ካልተደመሰሰ በስተቀር በድርድር ሰላም ይገኛል ማለት ሞኝነት ነው። ድርድር ለሕወሓት ጊዜ መግዣና የማዘናጊያ ስልት ነው ! #MinilikSalsawi