የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዘር ጥቃት ያደረሰበትን ያባረረውን አብራሪ የአቢሲኒያ በረራ አገልግሎትና ማሰልጠኛ ኩባንያ ጠራው

የአቢሲኒያ በረራ አገልግሎትና ማሰልጠኛ ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ካፒቴን ሰለሞን ግዛው እምቢተኛውን”አራሽ”ካፒቴን ዮሀንስ ተስፋዬን ወደ ስራ ጠሩ ።

“ከባርነት ነፃነት”ብሎ በአውሮፕላኑ መዘወሪያ ፋንታ እርፍ የጨበጠውን፤በበረራ ጎመናማ ዠርጋዳ ዩኒፎርም ምትክ አቡጀዲ ያጠለቀውን አሻፈረኝ ባይ ወጣት አብራሪ ወደተሰናበተው ኮክፒት ለመመለስ ወስነዋል።

ዮሀንስ በአየር መንገድ ቆይታው የበረራ ኅላፊው ካፒቴን በማንነቴ(በአማራነቴ)የተነሳ አነውሮኛል፤የሶስት ካፒቴኖች የሙያ ምስክርነት እያለኝ “አትችልም፤አትበርም፤ተከልሰህ እንደጀማሪ ተማሪ በተለማማጅነት ከሰው ጋር እንድትበር አደርግሀለሁ”ሲለኝ “አትችልም!ብዬ መታወቂያዬን ሰጥቼው ወጣሁ”ሲል ለአማራ ቴሌቪዥን ተናግሯል።አብራረሪው በኑሮ ክፉኛ ተጎሳቅሎ ይታያል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድለአማራ ቴሌቪዥን በፃፈው ደብዳቤ ዮሀንስ “ረዳት ፓይለት”እንጂ “ካፒቴን”አልነበረም ከማለቱም በላይ የችሎታ ችግር እንደነበረበት ገልጿል።

የካፒቴን ሰለሞን አቢሲኒያ የበረራ ኩባንያ የስራ ግብዣ የበረራ ክንፉን አውልቆ ጥሎ መሬት የተቀመጠውን አራሹን ፓይለት ዳግም ወደ ምስራቅ ፀሀይ መውጫ ሰማያት ላይ የመመለስ አቅም አለው።
አዋዜ