በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስፈን ውይይት እየተካሄደ ነው

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

በ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስፈን የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንዳለበት ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከማህበረሰብ የተውጣጡ 1500 ተሳታፊዎች በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት በሚካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ታድመዋል።

ዘንድሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ እና የተረጋጋ ለማድረግ ሁሉም ተዋናይ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል አቶ ደመቀ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ከመጡበት ተቋም እና አካባቢ በሚመነጩ ችግሮች እና መውጫ መንገዶች ዙሪያ ውይይቱ መቀጠሉን ከምክትል ጠ/ሚኒስትር ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Image may contain: 2 people, people on stage and indoor