ውዳሴ፡ በ 11 ጷጉሜዎች ለ16 ሺህ ሰዎች ነጻ የምርመራ አገልግሎት የሰጠው ማዕከል

ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል በጳጉሜ ወር ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል የነጻ ምርመራ ለማግኘት ፈልገው የሚመዘገቡት ሰዎችን ይመረምራል። ማዕከሉ ሲቲስካን፣ ኤም አር አይ፣ አልትራሳውንድ፣ ኤክስ ሬይና ሌሎች አገልግሎቶችን በአዲስ አበባ በሚገኙ ስድስት ቅርንጫፎች እየሰጠ ሲሆን፣ በሁሉም ቅርንጫፎቹ ሁሉንም የምርመራ አገልገሎት አቅም ለሌላቸው ሰዎች በነጻ እንደሚያቀርብ ለቢቢሲ ገልጿል።…