የእርቀ ሰላም ማብሰሪያ ጉባኤ በፍራንክፈርት ተካሄደ

በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አህጉረ ስብከት የእርስ በርስ ትውውቅ የሰላም ማብሠሪያ እና የአንድነት ልዩ ጉባኤ ዛሬ አካሄዱ። በጉባኤው ላይ በአውሮፓ ልዩ ልዩ ከተሞች የተቋቋሙ አገረ ስብከት ተጠሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተካፋይ ሆነዋል።…