ወባ መሰሉ ዴንጊ በሽታ በኢትዮጵያም መስፋፋት ጀምሯል

በመላው ዓለም በበርካታ ሀገራት በስፋት የሚታየው የዴንጊ ትኩሳት በኢትዮጵያ እምብዛም ስሙ ሲነሳ አይሰማም። በቅርቡ የተደረገ ጥናት ግን በሽታው በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉት በመተማ እና ሁመራ መታየቱን አመልክቷል። በአካባቢው በሽታውን እንደ ወባ የመውሰድ ችግር እንዳለ ጥናቱን በዋነኛነት ያካሄዱት የጎንደር ዩኒቨርስቲ ምሁር ይናገራሉ።…