በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ የዐቃቤ ሕግ እማኞች በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ተወሰነ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ የዐቃቤ ሕግ እማኞች በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ዛሬ ነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ወስኗል።

በመሆኑም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ጀምሮት የነበረው የምስክሮች አሰማም ሂደት እንደሚቀጥል ይጠበቃል ተብሏል።

ዐቃቤ ሕግ አምስት ምስክሮች መገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ታዳሚያን በሌሉበት በዝግ ችሎት፤ 16 እማኞች ደግሞ ከመጋረጃ ጀርባ እንዲመሰክሩለት የጠየቀ ሲሆን በግልፅ ችሎት ሊመሰክር የሚችል አንድም እማኝ አለማግኘቱ በተደጋጋሚ በችሎቶች ፊት ተናግሯል ።

ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሚቀጥለው ዓመት ማለትም ለጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. የወሰነው የጊዜ ቀጠሮ ተሰብሮ እንዲታይ ሊጠይቁ መሆኑን ጠበቆች ተናግረዋል።

መረጃው የባልደራሳ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ነው።