ከራያ ቆቦና አካባቢዋ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ150ሺ በዋግ ህምራ ዞን 18ሺ በላይ ደረሰ።

ከራያ ቆቦ፣ አላማጣ ና ዋጃ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ150ሺ በላይ እንደሚደርስ ተነግሯል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እታገኝ አዳነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከቀዬአቸው የተፈናቀሉት ዜጎች መካከል ወደ ዘመድ መጠጋት ያልቻሉት በወልዲያ እና መርሳ ጊዜያዊ መጠለያ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

አክለውም ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች የእለት ምግብ ፍራሽና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁስ እንደቀረበላቸው ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዋግ ህምራ ዞን አበርገሌ አካባቢ የተፈናቀሉ 18ሺ ዜጎች ያሉ ሲሆን ለእነዚህ ተፈናቃዮችም ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሯ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

እስካሁን በዘለቀው ጦርነትም በህወሀት ቁጥጥር ስር ያሉ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች በህይወት የመቆየት ስጋት እንዳለባቸው እየተነገረ ነው።