የኦሮሞ ፓርቲዎች መግለጫና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እስር

አምስት የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባን ጨምሮ ማክሰኞ ዕለት ያወጡት የጋራ መግለጫ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሰፊ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከመኾን አልፎ ብርቱ ተቃውሞ አጭሯል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለእስር ተዳርገው በወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ እንደሚገኙ መዘገቡ ሌላኛው አነጋጋሪ የኾነ ነጥብ ኾኗል።…