ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ ሕዝብ ቀርቶ ለህውሓትም ቢሆን ባለውለታ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ ሕዝብ ቀርቶ ለአሸባሪው ሃይልም ቢሆን ባለውለታ ነው” የምንልባቸው ምክንያቶች፦
አሳዬ ደርቤ
➖➖➖
➜አሸባሪው ከፌደራል መንግሥቱ ምንም ዓይነት ትዕዛዝ በማይቀበልበት ሁኔታ ከNGO ባለፈ መደበኛ በጀቱን እየላከ ይደግፋቸው ነበር
➜መቀሌ ላይ ተቀምጠው ውስኪ እየጠጡ በተለያዩ የሽብር ጥቃቶች ኢትዮጵያን ሲያምሷት ጠሚው ተመሳሳዩን በማድረግ ፈንታ አገሪቷን ትቶ ቤተ-መንግሥቱን ያሰማምር ነበር።
➜ህውሓት ክልላዊ ምርጫ አድርጎ ዳንኪራውን ሲረግጥ ጠሚው ችግኝ ይተክል ነበረ፤
➜ጌታቸው ረዳ በየቀኑ በቲቪ እየቀረበ “ጨቅላው” እና “ወፈፌው” ሲለው፥ ጠሚው “ደብረ ጽዮንን እገዙት” እያለ ይመልስ ነበር
➜ጁንታው በየሳምንቱ እሁድ ወታደራዊ ትርዒት ሲያሳይ ጠሚው ቀበናን እያለማና ቀይ ቀበሮ እያላመደ ነበረ
➜አሸባሪው ሃይል ከፌደራል ተሹመው የሚላኩ የሰሜን እዝ አዛዦችን በመጡበት አውሮፕላን እየሸኘ ያለመጠን ሲጨማለቅ፥ ጠሚው አቅሙን ከማሳየት ይልቅ አቅም አልባ መባልን መርጦ ነበረ፥
➜ትሕነግ ገዳም መግባት የሚገባቸውን አሮጊቶች መሳሪያ አስይዞ በቲቪ እያቀረበ ጥጋባቸውን ሲያሳይ፥ ጠሚው ከትሕነግ ጋር አስታርቁኝ” ከሚል ልመና ጋር ሽማግሌዎችን ሰብስቦ ወደ መቀሌ ይልክ ነበረ።
➜ከግብጽና ሱዳን ጋር መሥራታቸው አልበቃ ብሎ “ግድቡን ሽጦታል” እያሉ ሲያብጠለጥሉት ጠሚው በሩ ላይ ያለችውን ፒኮክ አሻግሮ እያዬ “ጌታ ይቅር ይበላችሁ” ይል ነበረ። 😁
➜እንዳጠቃላይ አሸባሪው ሃይል ሰሜን እዝን ጨፍጭፎ በቅራቅርና በራያ በኩል ወደ ሸገር መገስገስ እስኪጀምር ድረስ ጠሚው ፓርክ ልማት ላይ ነበረ፥
.
.
ስለዚህ የትግራ ሕዝብ ጠምዶ መያዝ ያለበት ከውስጡ የወጣውን አሸባሪ እንጂ አራት ኪሎ ያለውን መሪ አይደለም።

አሳዬ ደርቤ