አሜሪካ ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ እንድታስገባ ተጠይቀናል – በአሜሪካ ኮንግረስ የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኬረን ባስ

‹‹አሜሪካ ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ እንድታስገባ ተጠይቀናል በሚል የቀረበው ሃሳብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው›› – ዶክተር ማናዬ ዘገየ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር

(ኢ ፕ ድ) – ጥቂት የአሸባሪው ህወሓት ደጋፊዎች ያቀረቡትን ሃሳብ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አቋም በማስመስል አሜሪካ ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ እንድታስገባ ተጠይቀናል በሚል የቀረበው ሃሳብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጥስ እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር ዶክተር ማናዬ ዘገየ ገለጹ።

May be an image of 1 person and sittingዶክተር ማናዬ በአሜሪካ ኮንግረስ የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኬረን ባስ ሰሞኑን ከአፍሪካ ሕብረት ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ ላለው ችግር አሜሪካ ጦሯን እንድትልክ ውጭ ባሉ ኢትዮጵያውያን ተጠይቄያለሁ ማለታቸውን በመጥቀስ ፣ይህ አይነቱ ሀሳብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጥስ እንደሆነ አስታውቀዋል።

የኮንግረስ አባሏ በውጭ የሚገኙ ጥቂት የአሸባሪው ህወሓት ደጋፊዎች ያቀረቡትን ሀሳብ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አቋም በሚመስል መልኩ ማቅረባቸው ትክክል እንዳልሆነም አመልክተዋል።

የወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ሀሳቡ ምስራቅ አፍሪካን የማተራመስ እቅድ ያለው ነው ያሉት ዶክተር ማናዬ፣ ከቀጠናው አገራት አልፎም የተለያየ ፍላጎት ካላቸው ሃያላን አገራት ብርቱ ተቃውሞ ሊገጥማት እንደሚችል አመልክተዋል።

የኮንግረስ አባሏ ባቀረቡት ሃሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ማድረግ የሉዓላዊነት ህግ ይጥሳል። ብዙ የዓለም አገራት ትኩረት የሆነውን ምስራቅ አፍሪካን የማተራመስ ሴራ ነው ። ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊኖረው የሚችለው ምላሽም ከባድ ነው ብለዋል።
https://www.press.et/ama/?p=52297