በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው እየተለየ ሞት እስር ግፍና መከራ እየተፈፀመባቸው ነው

DW : ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ :- ሕፃናት እየሞቱብን ነው፤ ነፍሰ ጡር ሴቶች እህት ወንድሞቻችን እየተሰቃዩብን ነው ሥቃያችን፣ እንግልታችን እና መከራችን እየበዛ ነው:: በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው እየተለየ ሞት እስር ግፍና መከራ እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተገለፀ:: ኢትዮጵያኑ እንደሚሉት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ጭምር ቤታቸው እየተሰበረ ከነልጆቻቸው ወደእስር ቤት በመወርወር ላይ ናቸው:: በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ችግሩ እጅግ ውስብስብ እንደሆነና ዜጎችን ወደሃገራቸው የመመለስ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል::

ኢትዮጵያውያን “ሥቃያችን፣ እንግልታችን እና መከራችን እየበዛ ነው” እያሉ ነው። አንዲት ወጣት “ሕፃናት እየሞቱብን ነው፤ እህት ወንድሞቻችን እየተሰቃዩብን ነው። ነፍሰ ጡር ሴቶች እየተሰቃዩ ነው” ብላለች። አገሪቱ የስደተኞች ሕጓን ካሻሻለች በኋላ ጉዳዩ መወሳሰቡን በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ተናግረዋል