በኮንስትራክሽን፣ በመሬት አስተዳዳር፣ በገቢዎችና ጉምሩክ የመንግሥት ተቋማት ከፍተኛ ሙስና እየተፈፀመ መሆኑ ተሰምቷል

ሙስና በሦስት የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩ ተጠቆመበኢትዮጵያ በሦስት የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩን፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የተደረገ ጥናት አመለከተ፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሦስተኛው አገር አቀፍ የሙስና ቅኝት ጥናትና የፀረ ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት ማክሰኞ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደበት ወቅት እንደተገለጸው በኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ በመሬት አስተዳዳር፣ በገቢዎችና ጉምሩክ ከፍተኛ የሙስና ተጋላጭነት አለ፡፡

ኮሚሽኑ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ፣ በኢትዮጵያ የሙስና ሁኔታ በተመለከተ ከትግራይ ክልል ውጪ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ከተለያዩ የሕይወት መስክ ላይ የሚገኙ 6,627 ሰዎችን በጥናቱ መካተቱን ጠቁሞ፣ ‹ፍሮንቴር› የተባለ የጥናት ተቋም 130 ባለሙያዎች መድቦ እንደተካሄደ አስታውቋል፡፡

ጥናቱበአገሪቱአሁንላይያለውንየሙስናደረጃአመለካከትእንዳሳየና ሙስናንማጥፋትለዕድገትናለመልካምአስተዳደርወሳኝበመሆኑ፣የሙስናመከላከልተግባርትኩረትሊሰጠውእንደሚገባ በጥናቱትኩረት ተሰጥቶ እንደተሠራ ተጠቁሟል፡፡

የጥናቱ ውጤትም በአሁኑ ወቅት አገሪቱን ከሚፈትኑ ትልልቅ ችግሮች መካከል ሙስና በሦስተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ተነግሯል።

የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች አካባቢም የሙስና ታጋላጭነት መኖሩንም በመጠቆም፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ መቀየስ እንደሚገባቸው ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ድርጊቱን ለመቀነስና ለማጥፋት ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ያበራሩት የጥናቱ ቡድን መሪ ሀብታሙ ወንድሙ (ፕሮፌሰር) የተባሉ ምሁር ናቸው፡፡

‹‹ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ወጥ ለማድረግ ፖሊሲና ስትራቴጂ እያዘጋጀ ነው፤›› ያሉት ደግሞ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ ሲሆኑ፣ የተዘጋጀው ፖሊሲ በተለያዩ መድረኮች በዘርፉ ባለሙያዎችና በሚመለከታቸው አካላት በሚሰጡ ግብዓቶች ከበለፀገ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ እንደሚላክ አስታውቀዋል፡፡

የጥናቱን ውጤት እንደ ወሳኝ ግብዓት በመጠቀም ሙስናን የመከላከል ሥራውን ለማጠናከር ርብርብ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል፡፡

ምንጭ : ሪፓርተር