የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ማሰማራቱን የሚቃወሙት የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎችና የሶማሌ ክልል የኢትዮጵያ አካል መሆኑ ያልተዋጠላቸው ናቸው – ሙስጠፌ ሙሐመድ ኡመር

የሶማሌ ክልል የፌደራሉን ሠራዊት ለመደገፍ ልዩ ኃይል ማሰማራቱን የሚቃወሙት የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎችና የሶማሌ ክልል የኢትዮጵያ አካል መሆኑ ያልተዋጠላቸው ናቸው ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ተናገሩ።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሐመድ ኡመር፤ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ወደ ትግራይ መሰማራታቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

አቶ ሙስጠፌ ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት ከፌደራል መንግሥቱ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተከትሎ “በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው የሕግ ማስበር ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ” የክልሉን ልዩ ኃይል አባላት መላካቸውን አስታውቀዋል።

አክለውም ህወሓት ማዕከላዊ መንግሥቱን “ለማጥፋት” አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሙስጠፌ“ከፌደራል መንግሥቱ የቀረበልንን ጥያቄ ተከትሎ፣ ህወሓትን ለመቆጣጠር በሚካሄደው ትግል ላይ ለመሳተፍ ተንቀሳቅሰናል” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የልዩ ኃይል አባላቱን ከመላካቸው በፊት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መመካከራቸውን ገልፀዋል።

“እንዲህ አይነት ጉዳይ የክልሉ ነው። ውሳኔ ሰጪዎቹ እኛ ነን፤ ቢሆንም የሚመለከታቸውን አካላት በሙሉ በማማከር ነው ውሳኔውን ያሳለፍነው።”

ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ አክለውም የክልሉ ልዩ ኃይል በዚህ ጦርነት እንዳይሳተፍ በሚል ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ አካላትን “የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች እና የሶማሌ ክልል የኢትዮጵያ አካል መሆኑ ያልተዋጠላቸው” ሲሉ ገልፀዋቸዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል የሚካሄድ ሳይሆን በማዕከላዊ መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል የሚካሄድ ነው ሲሉ ገልፀውታል።

“የእኛን ወደ ስፍራው መንቀሳቀስ የሚቃወሙ ወገኖች ጦርነቱ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል አንደሆነ አስመስሎ ለማቅረብ ይፈልጋሉ። ይህ ጦርነት ግን በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የሚካሄድ ነው።”

አቶ ሙስጠፌ አክለውም የሶማሌ ልዩ ኃይል የማዕከላዊ መንግሥቱ አካል መሆኑን በማንሳት በጀቱን የሚያገኘው ከፌደራል መንግሥቱ በመሆኑ አገሩን መከላከል አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

“ልዩ ኃይሉ በጀቱን የሚያገኘው ከፌደራል መንግሥቱ ነው፤ ስለዚህ የፌደራል ሥርዓቱን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ የሶማሌ ልዩ ኃይል ወደ ትግራይ መዝመቱ በክልሉ የፀጥታ መዋቅር ላይ ክፍተት እንደማይፈጥርም ተናግረዋል።

“በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለው ኃይል ነው የላክነው። ስለዚህ የአካባቢያችንን ደኅንት የሚያሰጋ ምንም ክፍተት የለም” ሲሉ አስረድተዋል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሉን ወደ ስፍራው የላከው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ነው።

ከሶማሌ ክልል በተጨማሪ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ እና ሌሎችም ክልሎች የልዩ ኃይል አባሎቻቸው ከፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት ጎን እንዲቆሙ ወደ ጦር ግንባር በዚህ ሳምንት ልከዋል።

የፌደራል መንግሥቱ የህወሓት ኃይሎች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የሰሜን ዕዝን ማጥቃታቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ውስጥ ወታደራዊ ግጭት መቀስቀሱ ይታወሳል።

ከስምት ወራት ቆይታ በኋላ የፌደራል መንግሥት የክረምቱን የእርሻ ጊዜ ምክንያት በማድረግ የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ሠራዊቱን ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ከትግራይ ክልል ማስወጣቱን አሳውቋል።

የህወሓት ኃይሎች በበኩላቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ሰባት ቅድመ ሁኔታዎችን አቅርበው በአማራ እና በትግራይ ድንበሮች አካባቢ ወታደራዊ ግጭቶች አጋጥሟል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ከልዩ ኃይል አባላት ጋር