በኢትዮጵያ የዜጎች መብት እና የሕግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ

በፍራንክፈርት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቡራዩ እና አካባቢዋ ጥቃት ሰለባዎችን ለመዘከር ዛሬ ከተማ አስተዳደር ሕንጻ አካባቢ ተሰባስበው የጸሎት እና የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት አካሄዱ። ንጹሃን ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡበትን እና በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉበት ጥቃት ከባህላችን ያፈነገጠ እና ሰብአዊነት የጎደለው ነው ሲሉ አውግዘዋል።…