የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠንቀቅ ኃይል የምርጫ ታዛቢዎች ሥራ ጀመሩ

የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠንቀቅ ኃይል በእንግሊዝኛ ምህፃሩ (EASF) የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 ቀን፣ 2013 ዓ.ም የሚደረገውን የኢትዮጵያ ምርጫ የሚከታተሉ 28 ታዛቢዎቹን ዛሬ በይፋ ወደ ሥራ አሰማራ። ኃይሉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዐሥር አባል ሃገራት አሉት። ነገር ግን የሰኞውን ምርጫ የሚከታተሉ ታዛቢዎች የተውጣጡት ከስምንቱ ሃገራት ነው።…