የመንግስትና የምርጫ ቦርድ መዋቅር ያላያቸው እንደ ዜጋ መርጠው የማያውቁ ሕዝቦች በኢትዮጵያ መኖራቸው ተሰምቷል።

የአላጌ ማኅበረሰብ  በኢትዮጵያ ምርጫ ተሳትፈን አናውቀም ይላሉ

DW : ቁጥራቸው ከ10 ሺህ በላይ እንደሚገመት የሚገልጹት በአላጌ ግብርና ኮሌጅ ዙሪያ ኑሮአቸውን የመሰረቱት የማኅበረሰብ አካላት በኢትዮጵያ የምርጫ ተሳትፈን አናውቀም ይላሉ። ማኅበረሰቡ በ1973 ዓ.ም. ወላጆቻቸውን በጦርነት ላጡ ልጆች ማሳደጊያ ማዕከልነት በተመሰረተው የህጻናት አምባ እና በኋላም የግብርና ኮሌጅ ሆኖ አገልግሎት መስጠት ላይ ባለው አላጌ ግብርና ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ አካባቢ ኑሮያቸውን መስርተው ሲቆዩ የተካተቱበት የወረዳና የቀበሌ መዋቅር ባለመኖሩ እንደ ዜጋ መርጠው አያውቁም።ኮሌጁን የሚያስተዳድረው የግብርና ሚኒስቴር እኔ ኮሌጁን እንጂ ህዝቡን ስለማላስተዳድር የምርጫ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ የኔ ሃላፊነት አይደለም ሲል ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያነጋገርናቸው ባለስልጣን ስለጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል።