ሕይወታችን አደጋ ላይ ወድቋል – ከጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች

ከደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መንግሥት ለደረሰብን ችግር መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ጠየቁ። «ሕይወታችን አደጋ ላይ ወድቋል» በማለት ከጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ዛሬ ሀዋሳ በሚገኘው የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ደጃፍ በመሰባሰብ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ተፈናቃዮቹ አዛው ባሉበት የጉራፈርዳ ወረዳ እየተረዱ እንደሚገኙ ነው የማውቀው የሚለው የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ነዋሪዎቹ ቀደም ሲል ወደ መጡበት ዞን ስለመመለሳቸው አስከአሁን ያሳወቀው አካል እንደሌለ ገልጿል። DW