የጋራ ንቅናቄ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ መስራች አቶ ኦባንግ ሜቶ ከ16 ዓመታት ቆይታ በኋለ ጋንቤላ ገቡ።


የጋራ ንቅናቄ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ መስራች አቶ ኦባንግ ሜቶ ከ16 ዓመታት ቆይታ በኋለ ጋንቤላ ገቡ።

በጋንቤላ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደረሱ የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሰናይ አኳይን ጨምር ሌሎች የክልሉ ከፈተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

አቶ አቦንግ በአቀባበሉ ላይ እንደተናገሩት ትግላችን ለአንድ ብሄር ነፃነት ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ነፃነት ነው ብለዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሰናይ አኳይ በበኩላቸው ንቅናቄው መንግስት ያላያቸውን ክፍተቶች በመሳየት የሰብአዊ መብት እንዲከበር ለሚያደርገው እንቅስቃሴም ሆነ ለአጠቃላይ ዓለማው ስኬት ክልሉ የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

አቶ ኦባንግ በቆይታቸው ከክልሉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ አካለት ጋር ውይይት ያደረጋሉ።