ዩናይትድ ስቴትስ በሳምንቱ መጀመሪያ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ ቪዛን ጨምሮ የተለያየ ማዕቀብን መጣሏን ይፋ አድርጋለች። በትግራይ እየተፈጸመ ነው ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፍትሄ እስኪያገኝም ርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም እየተጠየቀ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገሪቱ ያሉ ችግሮችን ለማስወገድ እየሠራ መሆኑን በማመልከት አሜሪካ በውስጥ ጉዳዬ መግባቷን ካላቆመች ከመቶ ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጤን እገደዳለሁ ብሏል።
አሜሪካ ልታዝዘን አይገባም፤ ሉዓላዊነታችንን ተዳፍራለች የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፤ የውስጥ ችግራችሁን ከኃይል ይልቅ ሁሉን ያካተተ ውይይት በማድረግ ለመፍታት ሞክሩ የሚለው የውጭ ግፊት በአሉታዊ ጎኑ መታየት እንደሌለበት ይናገራሉ። ዶቼ ቬለ ማዕቀቡን፣ የኢትዮጵያ አቋምና ቀጣዩ የዋሽንግተን አዲስ አበባ ግንኙነት በተመለከተ ውይይት አካሂዷል። ሙሉውን ውይይቱ ከድምጽ ማዕቀፉ ያድምጡ። DW