6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ቀን እንደማይካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ይህ ያሳወቀው ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ባለበት መድረክ ላይ ነው።

ምርጫው ግንቦት 28 ይካሄዳል ተብሎ ነበር።

የመላ ኢትዮጵያ የድምፅ መስጫ ቀን ተመሳሳይ ይሁን ተባለ!!!

በፊት የአ.አ እና ድሬዳዋ ሰኔ 5; የሌላ ቦታ ግምቦት 28 ተብሎ ነበር፡፡

“…ድምጽ አሰጣጡ በተመሳሳይ ቀን እንዲሆን የተወሰነው ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትና ከፓርቲዎች በቀረበ ጥያቄ ነው” – ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ

የ6ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ በሁሉም አካባቢዎች በአንድ ቀን እንዲካሄድ መወሰኑን በተመለከተ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው መድረክ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቀደም ሲል የአገራዊ ምርጫው የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ቀን 2013 እንደሚሆን የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት እንደነበር አስታውሰዋል።

ነገር ግን ቦርዱ የድምጽ መስጫው ቀን በመላ አገሪቱ በተመሳሳይ ቀን እንዲካሄድ መወሰኑን በይፋ አሳውቀዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፥ የድምጽ አሰጣጡ በተመሳሳይ ቀን እንዲሆን ከውሳኔ የተደረሰው ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና ከፓርቲዎች በቀረበው ጥያቄ መሰረት መሆኑን አስረድተዋል።

ምርጫ ቦርድ ድምጽ መስጫው ቀን በ3 ሳምንት እንዲራዘም ፓርቲዎችን መጠየቁን የምርጫ ካርድ ምዝገባውና ሌሎች ስራዎች በተያዘላቸው ቀናት ባለመጠናቀቃቸው ምርጫው በተያዘለት ቀን አይካሄድም ተብሏል።

የድምፅ መስጫ ቀን ማራዘም ያስፈለገው ለምንድነው ?

ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቀን ሊራዘም እንደሚችል አስታውቋል።

ቦርዱ የምርጫው ጊዜ ቀድም ብሎ ከተያዘለት ጊዜ እስከ 3 ሳምንት በሚደርስ ጊዜ ነው እንደሚራዘም የገለፀው።

ምክንያት ብሎ ያቀረበው ፦

– የድምፅ መስጫ ወረቀት ህትመት የወሰደው ጊዜ በመኖሩ

– የመራጮች ምዝገባ የወሰደው ተጨማሪ ጊዜ በመኖሩ ይህን ለማስተካከል ነው።

ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገው ምክክር አሁንም የቀጠለ ሲሆን የሚደረስበትን ድምዳሜ ተከታትለን እናሳውቃለን።