ብልጽግና ፓርቲ በአዲስ አበባ የደረቅና የፈሳሽ ጭነት ባለንብረቶችን በግዳጅ ለምርጫ ገንዘብ እየተቀበለ መሆኑ ተሰማ

May be an image of text that says 'በተሽከረካሪ ብር1,000፡ለመዋጠት በተደረገው ሰምምነት ገቢ የሚሆነው የባንክ ሂሰብ ቁጥርAddis Ababa Prosperity Party Acct No. 1000327186721 ነው።'አዲስ አበባ፣ ለምርጫም ይፋዊ ዘረፋ? – Getachew Shiferaw
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ በከተማው ለሚገኙ የፈሳሽና ደረቅ ጭነት ባለሀብቶች ገንዘብ አዋጡ እያለ ነው። የደረቅ ጭነት ባለንብረቶች 1000 ብር፣ የፈሳሽ ጭነት ባለንብረቶች 5000 ብር እንዲከፍሉ ተብሏል።
በከተማዋ 12 ሺህ ያላነሱ የደረቅ ጭነት ማመላለሻዎች እንዳሉ ይታመናል። 12 ሚሊዮን ያላነሰ ብር ለማግኘት ክፈሉ እየተባሉ ነው። 5000 ያህል የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻዎች አሉ። በእያንዳንዳቸው 4000 ብር ክፈሉ ተብለዋል። 20 ሚሊዮን ማለት ነው። 32 ሚሊዮን ከፈሳሽና ደረቅ ጭነት ማመላለሻዎች ብቻ ለማግኘት እየወተወቱ ነው።
የጭነት ማመላለሻ ባለቤቶች በየ ስልካቸው የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የባንክ አካውንት ተልኮላቸዋል። በየቀኑ “አላስገባችሁም። አስገቡ” ይባላሉ። በዚህ ከአንዱ የኢትዮጵያ ክፍል ወደሌላው ተዟዙሮ መስራት ያልቻለ ባለሀብት ለምርጫ ሲሆን ግን የገንዘብ ቁጥርና የባንክ ቁጥር ልከው “ክፈል” ይሉታል።
ይህ እንግዲህ በጭነት መኪናዎች ላይ ብቻ የተጣለ መሆኑ ነው። በሌላው መስክም መሰል ግዴታ መጣላቸው የሚጠበቅ ነው። ከጭነት መኪናዎች 32 ሚሊዮን ከጠየቁ፣ ሌሎቹ ሲጨመሩ አዲስ አበባ በቢሊዮን እንድትከፍል ግዴታ ተጥሎባታል ማለት ነው። በዚህ ምርጫ ወቅትም ሕዝብን “ይህን እሰራልሃለሁ” ሳይሆን “ገንዘብ አምጣ” ሆኗል ጨዋታው።
Getachew shiferaw
May be an image of text that says 'Addis Ababa Prosperity Party Acct No. 1000327186721 10:01'